የተከበራችሁ የፌስ ቡክ ታዳሚዎቼ!
እንደሌሎች ሃይማኖቶች ሁሉ ያለአግባብ ሰውን የሚአክል ክቡር የአላህ ፍጡር ቀርቶ ለሰው ልጅ ግልጋሎት የተፈጠሩትን እንሣትን እንኳን ያለ አግባብ መግደል እስልምና አጥብቆ ይከለክላል።ለዝህም ነው እንሣትን እንኳን ለምግባችን ፍጆታ አሰቃይቶ ማረድን ወይም መግደል በጥብቅ የተተወገዘው።
በሁለቱም ታላላቅ እምነቶች በክርስትና እና እስልምና እንዲሁም ከነዚህ በፊትም በነበሩ ቅዱሳን መጽሃፎች ውስጥ ያላግባብ ሰውን መግደል በጥብቅ የተከለከለ መሆኑ ተጠቅሷል። እነዝህ ቅዱሳን መስሃፍት የፈጣሪያችን ቃል በመሆናቸው በምእመናን የተገበራሉ በካሃዴዎችና አስመሳዮች ግን ይጣሳሉ።