Monday, April 27, 2015

የግል መልእክት

                     
የተከበራችሁ የፌስ ቡክ ታዳሚዎቼ!

 ዛሬ ጾታ፤ሃይማኖት፤የፖለቲካ አመለካከታችንና ሌሎችም  ልዩነታቶቻችን ሳይገድቡን በየ በራሃው፡የወደቁ፤በየ ባህሩ ለሰመጡ፡በደቡብ አፍሪካ በህይወት ለተቃጠሉ፤በአረቡ አለም በየ ግለሰቦች ቤት ህይወታቸውን ላጡት ፤በተለይም አይሲስ በተባለው ቡዲን ችካኔ በተሞላበት ለታረዱትና በጥይት በተደበደቡት 30 ወንድሞቻችን ሃዘናችን ለመግለጽና በህይወት ያሉትንና በየመን የርበርስ ጦርነት ምክንያት መውጫ አጥተውና  በተለያዩ በየአለም ክፍሎች አሁንም ለሞት አደጋ  ተጋልጠው  በመንከራተት ላይ ያሉትን ጭምር ለማስታወስና የምንችለውን ሁሉ ለማድረግ ከያለንበት ድምጻችን እያሰማን ነው ነው።
                                                                             
እንደሌሎች ሃይማኖቶች ሁሉ ያለአግባብ ሰውን የሚአክል ክቡር የአላህ ፍጡር ቀርቶ ለሰው ልጅ ግልጋሎት የተፈጠሩትን እንሣትን እንኳን ያለ አግባብ መግደል እስልምና አጥብቆ ይከለክላል።ለዝህ ነው እንሣትን  እንኳን ለምግባችን  ፍጆታ  አሰቃይቶ ማረድን ወይም መግደል ብቅ የተተወገዘው።
                                                                      
በሁለቱም ታላላቅ እምነቶች  በክርስትና እና እስልምና እንዲሁም ከነዚህ በፊትም በነበሩ  ቅዱሳን መጽሃፎች  ውስጥ ያላግባብ ሰውን መግደል በጥብቅ የተከለከለ  መሆ ተጠቅሷል። እነዝህ ቅዱሳን መስሃፍት የፈጣሪያችን ቃል በመሆናቸው በምእመናን የተገበራ በካሃዴዎችና አስመሳዮች  ግን ይጣሳ
 
ይህንኑ በተመለከተ ቅዱስ ቁራን እንዲህ ይላል፡

ነፍስን የገደለ ሰው ሰዎቹ ሁሉ እንደገደለ ነው፤ ሕያው ያደረጋትም ሰው ሰዎቹን ሁሉ ሕያው እንዳደረገ ነው ማለትን ጻፍን፡፡ (ሱረቱል ማኢዳ 32)
                                                      

በቡካሪ ሐዲስ ውስጥ ነብዩ ሙሀመድ (..)

 ሙስሊም ባልሆኑ ንፁሐን ሰዎች ላይ ግድያ የፈፀመ ሰው የጀነትን እጣን አያሸትም(ቅጽ. 3, ሃዲስ # 2995) በማለት ይህንኑ አጠናክረዋል
 ኢትዮጵያ ሃገራችን በነብያችን ወቅት ለሀያ አመት ያህል በየቀኑ አምስት ጊዜ አዛን ያወጣ የነበረ የሙአዚኑ የነ ብላል ህገር ናት  ሴት ኢትዮጵያዊት ነቢዩ (..) መጀመሪያ ሲወለዱ አጎታቸው በደስታ ከባርነት ነጻ ያደረጉዋት  እና ወላጅ እናታቸው በስድስት አመት ዕድሜአቸው ሲሞቱባቸው ከዛ ጊዜ ጀምረው ሞግዚት በመሆን ነቢዩ እስኪሞቱ ድረስ አብረው ሲኖሩ ሲጠሩዋቸ እናቴ ብለው  ይጠሯት የነበር  የነ እሙል አይማን ወይም ባራካህ ሃገር ናት  ከሁሉም በላይ  ደግሞ የዛሬ 1400 አመት በፊት የገዛ ዜጎቻቸው ከሚያደርሱባቸው መከራ ስቃይ ለመሸሽ የሰው ልጅ በእምነቱ የማይበድልባት ሃገር ዳቹህ ተጠለሉ ተብለው  በነቢዩ  (..)     መለኮታዊ ምክር/ትዕዛዝ  የመጡትን  ሙስሊም ስደተኞችን  ተቀብላ ያስተናገደች አገር ናት።ዛሬ በአለም ላይ ካሉት ሀገሮች  የአረ አገሮችን ጨምሮ  ከዛሬዋ ሳውዲ አራቢያ  ውጭ መጀመሪያ ሙስሊሞች የኖርባት ብቸኛዋ  ሃገር ኢትዮጵያ ናት።ህም ነው የስሃቦሽ/የበዩ  (..)ታከትዮች  ወደ ሃገራችን ያደጉት ስደት በተለምዶ  የመጀመሪያ ስደት /ሂጅራ ተብሎ የሚጠራው።                                                       

 ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ነው የኢትዮጵያ ህዝብ በሃይማኖት ሳይለያይ ተቻችሎ እስከዛሬ የዘለቀው ።ለዚህም በነዚህ አይሲስ በተባሉት የሰው ዘር ጠላቶች ከታረዱት 30 ኢትዮፕያውያን ወስ አንዱ የሆነው  ሙስሊሙ ወንድማችን ጃማል ዓብዱራሂም በቂ ምስክር ነው። የጋራነታችን ለወደፊትም በዚሁ የቀጥ ዘንድ ከፋፋዮችንና አስመሳዮችን ለመወጋትም ሆነ ለስደታችን መንሴ  የሆኑትን ችግሮች  ሁሉ በጋራ ለመቅረፍ አንድነታችን አጠናክረን በጋራ መስራት የኖርብናል። ያለበለዚያ ችግራችን ሃዘናችን  በዚህ የሚያበቃ አይሆንም።

በአይሲስ ፣በደቡብ አፍሪካዊያን ፤በባህር ማእበል በየበረሃው በየመን የርስብርስ ጦርነት  ህወታቸውን ላጡት ነፍሳቸው ይማር : ተሰቦቻቸው ደግሞ ጽናቱን ይስጣቸው በማለት እንደ አንድ ሙስልም ኢትዮያዊ  እንደ አንድ እንደ የአ ዜጋ እንደ አንድ የአላህ ፍጡር የተሰማ ሃዘን እገልጻለሁ።

 አላህ ኢትዮጵያን ከነ ህዝቦቿ ይባርካት አሚን!!!

WORLD CLOCK - Move the cursor over the map to know the local time

Total Pageviews

CHUO Radio Archive