Thursday, October 30, 2008
Obama and the prospects for democracy in Ethiopia (Ethiopian review)
Somali premier reportedly accuses Ethiopia of "causing trouble"(Mareeg Online)
Tuesday, October 28, 2008
የኢዴአፓ የቀውስ ፖለቲካ (ቃልኪዳን አምባቸው) (Ethiopia Zare)
ቃልኪዳን አምባቸው
ኢዴአፓ-መድኅን በቀውስ ፖለቲካ ውስጥ መዘፈቁን የሚያሳዩ በቂ አስረጂዎች አሉ። ፓርቲው ውሉ ጠፍቶበታል። በአንድ በኩል የገዥው ፓርቲ ዕድገት አብሳሪ መሆንን ይሻል። የኢህአዴግን መጠንከር፣ በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ማግኘት፣ በመጪው ምርጫ አሸናፊ እንደሚሆንና ሌሎችንም የምንሰማው ከኢህአዴግ የህዝብ ግንኙነት ቢሮ ሳይሆን ከኢዴአፓ-መድኅን የፓርቲዎች የግምገማና የልኬት ቤተ-ሙከራ ነው። ኢዴአፓ-መድኅን ይህን ቢያደርግ በእርግጥ ከልካይ የለበትም።
በአንፃሩ ደግሞ ተቃዋሚዎች መፍረክረካቸውን፣ በኢትዮጵያ ፖለቲካ አወንታዊ ሚና መጫወት የሚችል የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት ያለመኖሩን፣ ተቃዋሚዎች በመጪው ምርጫ ሊያሸንፉ እንደማይችሉም ሆነ በደፈናው የተቃዋሚዎችን ጉድለትና ድክመት፣ በመራር መግለጫዎች ሲያዥጎደጉድ የምንሠማው ራሱን የተቃዋሚዎች እንደራሴ አድርጎ ከሾመው ኢዴአፓ-መድኅን ነው። ይህን ጊዜ ነው እንግዲህ ፓርቲው ውሉ ጠፍቶበታል የሚያሰኘው።
የኢዴአፓ-መድኅን የቀውስ መዘውር በዚህ ብቻ አይገደብም፤ በኢዴአፓ-መድኅን የልኬት ቤተ-ሙከራ የተገመገመው የኢትዮጵያ ህዝብም ”አሉታዊ ሚና …” ያለው በሚል ተፈርጇል። ”ሕገ-መንግሥቱ በብዙ መልኩ ጥሩ ሆኖ ተገኝቷል …” የሚለው የኢዴአፓ-መድኅን የምርምርና የጥናት ግምገማ በአንድ ጉዳይ ላይ ግን ያብጠለጥለዋል፤ ለጠቅላይ ሚንስትሩ የሥልጣን ገደብ ወይም ለምን ያህል ጊዜ ሥልጣን ላይ መቆየት እንደሚችሉ መወሰን ነበረበት ይለናል። ከኢዴአፓ-መድኅን የመሪነት ዙፋን ነቅነቅ ማለትን ለማይደፍሩት ለአቶ ልደቱ አያሌው፣ ፓርቲው መላ መምታት እንዳለበት ግን ግምገማው አልተወያየበትም። በእርግጥ ኋላ ላይ ፓርቲው ለተዘፈቀበት የቀውስ ፓለቲካ ዋነኛው ምክንያት የከፊል አመራሮቹ ግላዊ ቀውስ መሆኑን የምንሞግተው ቢሆንም፤ አቶ ልደቱ ”ሥልጣን ይልቀቁ” ማለትን እንጂ ሥልጣን ልልቀቅ የማይሉ የአሮጌው ሥርዓት አራማጅ እንጂ የለውጥ ሐዋርያ አለመሆናቸውን መገንዘብ ብዙ አይቸግርም።...more...
Ethiopia blames Somali leadership for peace failures(AFP)
NAIROBI (AFP) — Ethiopia, whose forces toppled an Islamist regime in Mogadishu two years ago, on Tuesday blamed the failure to restore stability in Somalia on the transitional rulers it helped bring to power.
"Somalia's problems are not security, but political," said Foreign Minister Seyoum Mesfin at a meeting of governments in the region focused on Somalia....more..
Monday, October 27, 2008
“ኢህአዴግ ራሱን ብቻ ለመጪው ምርጫ እያዘጋጀ ነው” የምክክር መድረክ(Ethiopia Zare)
Ethiopia Zare (እሁድ ጥቅምት 16 ቀን 2001 ዓ.ም. October 26, 2008)፦ የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ጥረት የማዕዘን ደንጋይ የሆኑ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከገዥው ፓርቲ ጋር በ1998 ዓ.ም. የጀመሩት ውይይት ተቋርጦ “ገዢው ፓርቲ ራሱን ብቻ ለመጪው ምርጫ እያዘጋጀ ነው” ሲል መድረክ ለዲሞክራሲያዊ ምክክር በኢትዮጵያ አስታወቀ።
መድረኩ ይህን ያስታወቀው በኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ጽሕፈት ቤት ትናንት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ሲሆን፣ በመግለጫው “በሀገራችን ዘላቂ ሠላም ለማስፈን በውጭም በሀገር ውስጥም ከሚንቀሳቀሱት ከሁሉም ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ውይይት የሚካሄድበት ሁኔታ ይመቻቻል፤ እንደዚሁም በ2002 ዓ.ም. ለሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ አስፈላጊው ቅድመ ሁኔታዎች ማለትም፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከመንግሥት ድጐማ የሚያገኙበት፣ የተዘጉ ጽ/ቤቶቻቸው የሚከፈቱበት እና የታሰሩ አባሎቻቸው የሚፈቱበት እርምጃ ይወስዳል” የሚል በፕሬዝዳንቱ ንግግር ውስጥ እንዲካተት ያቀረብነው ሃሳብ ለውይይት እንኳን እንዳይቀርብ በምክትል አፈጉባዔዋ ውድቅ ሆኖብናል ሲሉ በመግለጫው አስታውቀዋል።
በሀገራችን በአስከፊ ሁኔታ በገጠርም በከተማም እየደረሰ ስላለው ረሃብ የሚያወላዳ መፍትሔ የሚገኝበት ሁኔታ ይመቻቻል፣ የኢትዮጵያ ጦር ከሶማሊያ በአስቸኳይ ስለሚወጣበት ሁኔታ አስፈላጊው እርምጃ ሁሉ የሚወሰድ ይሆናል።
በጋዜጣዊ መግለጫው አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከኦፌዴን፣ ከሶማሌ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ኃይሎች ቅንጅት አቶ አለን ናስር፣ በግል ደግሞ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ሲገኙ የዓረና ትግራይ ለዲሞክራሲና ለሉዓላዊነት ተወካዮች አልተገኙም።
የዓረና ተወካዮች እነ አቶ ስዬ አብርሃ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ያልተገኙት ባጋጠማቸው ኀዘን መሆኑን የጠቆሙት ፕሮፌሠር በየነ ጴጥሮስ፤ መግለጫው እነሱም የተስማሙበት የምክክር መድረኩ አቋም ነው ብለዋል።Source Ethiopia Zare
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 27 ሚሊዮን ዶላር ተጭበረበረ (Ethiopia Zare)
Ethiopia Zare (እሁድ ጥቅምት 16 ቀን 2001 ዓ.ም. October 26, 2008)፦ በዚህ ሣምንት ኒውዮርክ (አሜሪካ) ከሚገኘው ሲቲ ባንክ ውስጥ ገንዘብነቱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሆነ 27 ሚሊዮን ዶላር ተጭበረበረ። ገንዘቡን ሲያጭበረብሩ የተያዙት ናይጄሪያውያን በቁጥጥር ስር ውለዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በራሱ አካውንት ቁጥር በሲቲ ባንክ ተቀማጭ ገንዘብ ያለው ሲሆን፣ ይህንን ገንዘብ ሦስት ናይጄሪያውያን እንዳጭበረበሩት ባለፈው ሣምንት ኀሙስ ተገልጿል።
ባንኩ እንደገለፀው ከሲቲ ባንክ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን አጭበርባሪዎቹ እንዲታወቁ ያደረገ ሲሆን፣ የገንዘቡ መጭበርበርም በኢትዮጵያ ሀብት ላይ ምንም ለውጥ እንደማያመጣ ገልጸዋል።
ምክንያቱም ችግሩ የተፈጠረው በኢትዮጵያ በኩል ባለመሆኑና በዚሁ ጉዳይ ላይም ከሲቲ ባንክ ጋር በመነጋገር ከስምምነት ላይ በመድረሱ ነው።
እስከ ኀሙስ ጥቅምት 13 ቀን 2001 ዓ.ም. ድረስ 10 ሚሊዮን ዶላር ወደ ብሔራዊ ባንክ አካውንት ውስጥ መግባቱን ገልጿል።
በኢትዮጵያ የሚገኙ ብሔራዊ ባንክን ጨምሮ የመንግሥት እና የግል ባንኮች ከውጭ ባንኮች ጋር አብሮ ከመሥራታቸውም በተጨማሪ አካውንት አላቸው።Source Ethiopia Zare
ከምርጫ 97 በኋላ በተፈጠረው ግጭት የተሳተፉ ሊጠየቁ ይገባል (ፕ/ር ዓለማየሁ ገ/ማርያም)(Ethiopia Zare)
ባለፈው ሣምንት የኢትዮጵያን ውስጣዊ የፀጥታ ሁኔታ ማዘመን “Moderenizing Internal Security In Ethiopia” የሚል ይፋዊ ሪፖርት ተሰራጭቶ ነበር። ሪፖርቱ በጡረተኛው የብሪታኒያ ኮሎኔል ሚካኤል ዲዋር ሰኔ ወር 2000 ዓ.ም. ላይ የተዘጋጀ ሲሆን ቅኝቱ፣ ግኝቱና የመፍትሔ ሃሳቡ ስኬትን በሚያሳይ መልኩ የተቀመጠ ነው። ለፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶችም ምክር ይሰጣል። ኮሎኔል ዲዋር እንደሚገልፁት በጥናቱ ላይ በለንደን የኢትዮጵያ አምባሣደርና በኢትዮጵያ የቀድሞ የብሪታኒያ አምባሳደርን ጨምሮ በርካታ ባለሙያዎች ከግንቦት 2007 እ.ኤ.አ. ጀምሮ መሳተፋቸውን ይጠቅሳል።...more..
Muslims applaud Colin Powell for defending them (Chigago Sun-Times)
Thursday, October 23, 2008
SKorea arrests Nigerians over massive banking scam (Yahoo news)
Untapped Talents of Educated Immigrants (Washington Post)
Tuesday, October 21, 2008
Five Reasons for Ethiopian-Americans to Support Obama(Tadias)
Botswana's Mogae wins $5m prize (BBC)
Sunday, October 19, 2008
Powell endorses Obama for president(msnbc)
“The really right answer is what if he is?” Powell said, praising the contributions of millions of Muslim citizens to American society.
“I look at these kind of approaches to the campaign, and they trouble me,” Powell said. “Over the last seven weeks, the approach of the Republican Party has become narrower and narrower.” ...read more..
Saturday, October 18, 2008
የትምህርት ጥራት መጓደል (Ethiopia Zare)
እንደ ፕሮፌሠር ባደግ ገለፃ ከትምህርት ጥራት መለኪያዎች መካከል የአስተማሪዎች ብቃትና የትምህርት ማስተማሪያ አጋዦች (ቤተ መጻሕፍት፣ ኢንተርኔትና የመሳሰሉት) ይጠቀሳሉ፤ የትምህርት ጥራት መጓደል ከተማሪዎች የተወዳዳሪነት አቅም ማነስ ጋር የሚያያዝ ሲሆን፣ መንግሥት ከመጠን በላይ ተማሪ በመቀበል ላይ ማተኮር ሳይሆን ከተቋማቱ ጋር ተመጣጣኝ ተማሪ በመቀበል ተወዳዳሪ ማድረግ ላይ ትኩረት ሊሰጥ ይገባል ይላሉ። ...more..
Friday, October 17, 2008
British minister withholds aid as Ethiopia hides famine victims(TIMESONLINE))
After visiting the Somali region and hearing the testimony of aid organisations as well as evidence of attempts by the authorities to hide the scale of the crisis, Mr Alexander told the Ethiopian Prime Minister, Meles Zenawi, that he had reconsidered. “In light of our continued concerns, I said I was now not prepared to make a multi-annual commitment,” Mr Alexander said. ...more..
Ethiopia Rejects Somalia Withdrawal Timetable (VOA)
On World Food Day, 17 Million People Face Starvation in the Horn of Africa (care))
Thursday, October 16, 2008
Troop pull-out leaves government on brink (Sunday hearald)
Saturday, October 11, 2008
From 'Love Kitten' to child literacy(CNN)
"Children could imagine everything from books -- connections to other cultures, to other people, to other children, and to the universe at large," recalls Gebregeorgis. "..more..
Monday, October 6, 2008
8 Kenyans back from Ethiopia want police charged(Daily Nation)
Commentary: The End of Pax Zenawi in Somalia - By Alemayehu G. Mariam(HAROWO)
Sunday, October 5, 2008
Ethiopia returns to Kenya suspected militants(Reuters)
The groups say they were kept in jails rife with torture that some campaigners called an "African Guantanamo", drawing a parallel with suspects held at the U.S. base at Guantanamo Bay in Cuba under the U.S.-led "war on terror"....more..
"Why Am I still Here?" (HRW)
ኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካ በዲሞክራሲ ገጽታ (ከፕ/ር አለማየሁ ገ/ማርያም)[Ethiopia are]
ፕሮፌሠር አለማየሁ ገ/ማርያም
ኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካን ከሚለይዋቸው ገጽታዎች ዋነኛው በዲሞክራሲ ግንባታ ረገድ እየተጓዙበት ያለው መንገድ ነው። በደቡብ አፍሪካ የዲሞክራሲ መገለጫ የሆነው የህዝብ መንግሥት፣ በህዝብ የተመረጠ መንግሥትና ለህዝብ የሚሠራ መንግሥት የመኖሩ ጉዳይ ነው። (Government of the people by people and for the people) በኢትዮጵያ ያለው የአገዛዝ ሥርዓት መገለጫ ግን የዲሞክራሲ ገጽታ አለው ለማለት ይከብዳል። ምክንያቱም ከዲሞክራሲ መገለጫው ይልቅ ጥቂት ግለሰቦች በሥልጣን ላይ የሚቆዩበትና የህዝብን ሀብት እንደፈለጉ የሚያደርጉበት ሁኔታ የበለጠ ይጐላልና።...more..