Saturday, October 18, 2008

የትምህርት ጥራት መጓደል (Ethiopia Zare)

..የኢንተርናሽናል ሊደርሺፕ ተቋም መሥራችና ፕሬዝዳንት ፕሮፌሠር ባደግ በቀለ፣ ከሪፖርተር ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ፣ በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራት መጓደል እንደሚታይ ገልፀዋል። ለጥራት መጓደሉም ከፍተኛ ነጥብ ያመጡ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲው በመምህርነት እንዲያስተምሩ መደረጉ የመምህራን እጥረት መሆኑን ይገልፃሉ። በሌላው ዓለም የቢ.ኤ. ዲግሪ ያለው የማስተርስ ዲግሪን አያስተምርም፤ እንዲሁም የማስተርስ ተማሪ የፒ.ኤች. ዲግሪን አያስተምርም። በኢትዮጵያ ግን ይኼን መመልከቱ የተለመደ ከመሆኑም በላይ ለትምህርት ጥራት መጓደሉ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ነው ያመለከቱት።

እንደ ፕሮፌሠር ባደግ ገለፃ ከትምህርት ጥራት መለኪያዎች መካከል የአስተማሪዎች ብቃትና የትምህርት ማስተማሪያ አጋዦች (ቤተ መጻሕፍት፣ ኢንተርኔትና የመሳሰሉት) ይጠቀሳሉ፤ የትምህርት ጥራት መጓደል ከተማሪዎች የተወዳዳሪነት አቅም ማነስ ጋር የሚያያዝ ሲሆን፣ መንግሥት ከመጠን በላይ ተማሪ በመቀበል ላይ ማተኮር ሳይሆን ከተቋማቱ ጋር ተመጣጣኝ ተማሪ በመቀበል ተወዳዳሪ ማድረግ ላይ ትኩረት ሊሰጥ ይገባል ይላሉ። ...more..

WORLD CLOCK - Move the cursor over the map to know the local time

Total Pageviews

CHUO Radio Archive