ባለፈው ሣምንት የኢትዮጵያን ውስጣዊ የፀጥታ ሁኔታ ማዘመን “Moderenizing Internal Security In Ethiopia” የሚል ይፋዊ ሪፖርት ተሰራጭቶ ነበር። ሪፖርቱ በጡረተኛው የብሪታኒያ ኮሎኔል ሚካኤል ዲዋር ሰኔ ወር 2000 ዓ.ም. ላይ የተዘጋጀ ሲሆን ቅኝቱ፣ ግኝቱና የመፍትሔ ሃሳቡ ስኬትን በሚያሳይ መልኩ የተቀመጠ ነው። ለፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶችም ምክር ይሰጣል። ኮሎኔል ዲዋር እንደሚገልፁት በጥናቱ ላይ በለንደን የኢትዮጵያ አምባሣደርና በኢትዮጵያ የቀድሞ የብሪታኒያ አምባሳደርን ጨምሮ በርካታ ባለሙያዎች ከግንቦት 2007 እ.ኤ.አ. ጀምሮ መሳተፋቸውን ይጠቅሳል።...more..