Tuesday, October 28, 2008

የኢዴአፓ የቀውስ ፖለቲካ (ቃልኪዳን አምባቸው) (Ethiopia Zare)

ቃልኪዳን አምባቸው

ኢዴአፓ-መድኅን በቀውስ ፖለቲካ ውስጥ መዘፈቁን የሚያሳዩ በቂ አስረጂዎች አሉ። ፓርቲው ውሉ ጠፍቶበታል። በአንድ በኩል የገዥው ፓርቲ ዕድገት አብሳሪ መሆንን ይሻል። የኢህአዴግን መጠንከር፣ በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ማግኘት፣ በመጪው ምርጫ አሸናፊ እንደሚሆንና ሌሎችንም የምንሰማው ከኢህአዴግ የህዝብ ግንኙነት ቢሮ ሳይሆን ከኢዴአፓ-መድኅን የፓርቲዎች የግምገማና የልኬት ቤተ-ሙከራ ነው። ኢዴአፓ-መድኅን ይህን ቢያደርግ በእርግጥ ከልካይ የለበትም።

በአንፃሩ ደግሞ ተቃዋሚዎች መፍረክረካቸውን፣ በኢትዮጵያ ፖለቲካ አወንታዊ ሚና መጫወት የሚችል የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት ያለመኖሩን፣ ተቃዋሚዎች በመጪው ምርጫ ሊያሸንፉ እንደማይችሉም ሆነ በደፈናው የተቃዋሚዎችን ጉድለትና ድክመት፣ በመራር መግለጫዎች ሲያዥጎደጉድ የምንሠማው ራሱን የተቃዋሚዎች እንደራሴ አድርጎ ከሾመው ኢዴአፓ-መድኅን ነው። ይህን ጊዜ ነው እንግዲህ ፓርቲው ውሉ ጠፍቶበታል የሚያሰኘው።

የኢዴአፓ-መድኅን የቀውስ መዘውር በዚህ ብቻ አይገደብም፤ በኢዴአፓ-መድኅን የልኬት ቤተ-ሙከራ የተገመገመው የኢትዮጵያ ህዝብም ”አሉታዊ ሚና …” ያለው በሚል ተፈርጇል። ”ሕገ-መንግሥቱ በብዙ መልኩ ጥሩ ሆኖ ተገኝቷል …” የሚለው የኢዴአፓ-መድኅን የምርምርና የጥናት ግምገማ በአንድ ጉዳይ ላይ ግን ያብጠለጥለዋል፤ ለጠቅላይ ሚንስትሩ የሥልጣን ገደብ ወይም ለምን ያህል ጊዜ ሥልጣን ላይ መቆየት እንደሚችሉ መወሰን ነበረበት ይለናል። ከኢዴአፓ-መድኅን የመሪነት ዙፋን ነቅነቅ ማለትን ለማይደፍሩት ለአቶ ልደቱ አያሌው፣ ፓርቲው መላ መምታት እንዳለበት ግን ግምገማው አልተወያየበትም። በእርግጥ ኋላ ላይ ፓርቲው ለተዘፈቀበት የቀውስ ፓለቲካ ዋነኛው ምክንያት የከፊል አመራሮቹ ግላዊ ቀውስ መሆኑን የምንሞግተው ቢሆንም፤ አቶ ልደቱ ”ሥልጣን ይልቀቁ” ማለትን እንጂ ሥልጣን ልልቀቅ የማይሉ የአሮጌው ሥርዓት አራማጅ እንጂ የለውጥ ሐዋርያ አለመሆናቸውን መገንዘብ ብዙ አይቸግርም።...more...

WORLD CLOCK - Move the cursor over the map to know the local time

Total Pageviews

CHUO Radio Archive