የተከበራችሁ የፌስ
ቡክ ታዳሚዎቼ!
ዛሬ ጾታ፤ሃይማኖት፤የፖለቲካ አመለካከታችንና ሌሎችም ልዩነታቶቻችን ሳይገድቡን በየ በራሃው፡የወደቁ፤በየ ባህሩ ለሰመጡ፡በደቡብ አፍሪካ በህይወት ለተቃጠሉ፤በአረቡ አለም በየ ግለሰቦች ቤት ህይወታቸውን ላጡት ፤በተለይም አይሲስ በተባለው ቡዲን ችካኔ በተሞላበት ለታረዱትና በጥይት በተደበደቡት 30 ወንድሞቻችን ሃዘናችን ለመግለጽና በህይወት ያሉትንና በየመን የርበርስ ጦርነት ምክንያት
መውጫ አጥተውና በተለያዩ በየአለም ክፍሎች አሁንም ለሞት አደጋ ተጋልጠው በመንከራተት ላይ ያሉትን ጭምር ለማስታወስና የምንችለውን ሁሉ ለማድረግ ከያለንበት ድምጻችን እያሰማን ነው ነው።
እንደሌሎች ሃይማኖቶች ሁሉ ያለአግባብ ሰውን የሚአክል ክቡር
የአላህ
ፍጡር
ቀርቶ
ለሰው
ልጅ
ግልጋሎት
የተፈጠሩትን እንሣትን እንኳን ያለ አግባብ መግደል እስልምና አጥብቆ ይከለክላል።ለዝህም
ነው
እንሣትን
እንኳን ለምግባችን ፍጆታ አሰቃይቶ ማረድን
ወይም መግደል በጥብቅ
የተተወገዘው።
በሁለቱም ታላላቅ እምነቶች በክርስትና እና እስልምና እንዲሁም ከነዚህ በፊትም በነበሩ ቅዱሳን መጽሃፎች ውስጥ ያላግባብ ሰውን መግደል በጥብቅ የተከለከለ መሆኑ
ተጠቅሷል።
እነዝህ
ቅዱሳን
መስሃፍት
የፈጣሪያችን ቃል በመሆናቸው በምእመናን የተገበራሉ
በካሃዴዎችና አስመሳዮች ግን ይጣሳሉ።
ይህንኑ
በተመለከተ ቅዱስ ቁራን እንዲህ ይላል፡
ነፍስን የገደለ ሰው ሰዎቹ ሁሉ እንደገደለ ነው፤ ሕያው ያደረጋትም ሰው ሰዎቹን ሁሉ ሕያው እንዳደረገ ነው ማለትን ጻፍን፡፡ (ሱረቱል ማኢዳ 32)
በቡካሪ ሐዲስ ውስጥ ነብዩ ሙሀመድ (አ.ራ.ይ)
“ሙስሊም ባልሆኑ ንፁሐን ሰዎች ላይ ግድያ የፈፀመ ሰው የጀነትን እጣን አያሸትም” (ቅጽ. 3,
ሃዲስ
# 2995)። በማለት ይህንኑ አጠናክረዋል
ኢትዮጵያ ሃገራችን በነብያችን ወቅት ለሀያ አመት ያህል በየቀኑ አምስት ጊዜ አዛን ያወጣ የነበረ የሙአዚኑ የነ ብላል ህገር ናት የሴት ኢትዮጵያዊት
ነቢዩ (አ.ራ.ይ) መጀመሪያ ሲወለዱ አጎታቸው
በደስታ ከባርነት ነጻ
ያደረጉዋት እና
ወላጅ እናታቸው በስድስት
አመት ዕድሜአቸው ሲሞቱባቸው
ከዛ ጊዜ ጀምረው
ሞግዚት በመሆን ነቢዩ
እስኪሞቱ ድረስ አብረው
ሲኖሩ ሲጠሩዋቸው
እናቴ ብለው
ይጠሯት የነበር የነ እሙል
አይማን ወይም ባራካህ
ሃገር
ናት ከሁሉም በላይ ደግሞ የዛሬ 1400 አመት በፊት የገዛ ዜጎቻቸው ከሚያደርሱባቸው መከራና ስቃይ ለመሸሽ የሰው ልጅ በእምነቱ የማይበድልባት ሃገር ሄዳቹህ ተጠለሉ ተብለው በነቢዩ (አ.ራ.ይ) መለኮታዊ
ምክር/ትዕዛዝ የመጡትን ሙስሊም ስደተኞችን ተቀብላ ያስተናገደች አገር ናት።ዛሬ በአለም ላይ ካሉት ሀገሮች የአረብ አገሮችን ጨምሮ ከዛሬዋ ሳውዲ አራቢያ ውጭ መጀመሪያ
ሙስሊሞች
የኖርባት
ብቸኛዋ ሃገር ኢትዮጵያ ናት።ለዚህም ነው የስሃቦሽ/የበዩ (አ.ራ.ይ)ታከትዮች ወደ ሃገራችን ያደረጉት ስደት በተለምዶ
የመጀመሪያ ስደት /ሂጅራ ተብሎ የሚጠራው።
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ነው የኢትዮጵያ ህዝብ በሃይማኖት ሳይለያይ ተቻችሎ እስከዛሬ የዘለቀው ።ለዚህም
በነዚህ አይሲስ በተባሉት
የሰው ዘር ጠላቶች
ከታረዱት 30 ኢትዮፕያውያን ወስጥ
አንዱ የሆነው ሙስሊሙ
ወንድማችን ጃማል ዓብዱራሂም
በቂ ምስክር ነው።
የጋራነታችን ለወደፊትም በዚሁ የቀጥል ዘንድ ከፋፋዮችንና አስመሳዮችን ለመወጋትም ሆነ ለስደታችን መንሴ የሆኑትን
ችግሮች ሁሉ በጋራ ለመቅረፍ አንድነታችን አጠናክረን በጋራ መስራት የኖርብናል። ያለበለዚያ ችግራችንና
ሃዘናችን በዚህ የሚያበቃ አይሆንም።
በአይሲስ
፣በደቡብ አፍሪካዊያን
፤በባህር ማእበል ፣
በየበረሃውና በየመን
የርስብርስ ጦርነት ህወታቸውን
ላጡት ነፍሳቸው ይማር
: ለቤተሰቦቻቸው
ደግሞ ጽናቱን ይስጣቸው
በማለት እንደ አንድ
ሙስልም ኢትዮጵያዊ እንደ
አንድ እንደ የአለም ዜጋ እንደ አንድ የአላህ ፍጡር የተሰማኝ
ሃዘን እገልጻለሁ።
አላህ ኢትዮጵያን ከነ ህዝቦቿ ይባርካት ፤ አሚን!!!