ይሄይስ አእምሮ
እኛ ኢትዮጵያውያን በቁም መመሰጋገን ወይንም መወዳደስ ብዙውን ጊዜ ያቅተናል – ምክንያቱን በውል አላውቅም፡፡ ምናልባት ውዳሤ ከንቱ እንዳይመስልብን ከመፍራት አኳያ ይመስለኛል ሰውን በሕይወት ዘመኑ – እንደፈረንጆቹ – የማወደስ ባህላችን እስከዚህም የሆነው – ይህን የይሉኝታ እሥረኛ የሆነ ልማዳችንን ቅድስና ለመስጠት ታዲያ “ሆድ ያመስግን”፤ “ሙያ በልብ” የመሳሰሉ አባባሎች አሉን፡፡ ምናልባት “አመስጋኝ አማሳኝ” እንደሚባለው ተመስጋኙ የልብ ልብ እንዳይሰማውና እንዳይታበይ ታብዮም እንዳይበላሽብን ከመሥጋት አንጻርም ሊሆን ከቻለ የማናመሰግነው ይህንንም አላውቅም፡፡ ግን አንድ ሰው ከሞተ በኋላ የምሥጋናና የሙገሣ ዶፍ ከማዝነብ – ላያየው – በቁም እያለም አክብሮትንና ፍቅርን መግለጽ መልካም አጋጣሚ ይመስለኛል፡፡ ይህን በጎ ምግባር ብንለምደው አንድ ሰው ከዚህች ምድር ሲሰናበት ወይም ከተሰናበተ በኋላ በውዳሤ ለማንበሽበሽም ሆነ በዕንባ ጎርፍ ለመዘከር ከመጣደፍ የተሻለ አግባብነትና ጠቀሜታ አለው፡፡read more...