ግንቦት 25፣ 2002 በፕሮፌሰር ይስሃቅ ኤፍሬምና በአትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ የሚመራው የሽማግሌዎች ኮሚቴ መለስ ዜናዊን አጊኝቶ አነጋግሮት ነበር። ሽምግልናው ተቃዋሚዎችንና የመለስን ቡድን ማቀራረብ የሚል ነው። ኮሜቴው በራሱ ተነሳሽነት ተንቀሳቀሰ ወይስ በመለስ የእጅ አዙር ግፊት አይታወቅም። መለስ ዜናዊ ግን ለሽማግሌዎቹ ኮሚቴ የሚከተለውን ቃል ሰጥቶአል።
1. ተቃዋሚዎች ‘ምርጫው ተጭበርብሮአል’ ብለው ወደ ፍርድ ቤት ለመሄድ የሚያስቡትን በመተው፣ የኢህአዴግን ማሸነፍ በይፋ እንዲቀበሉ።
2. ይህን ከፈፀሙ አንዳንድ የሚንስትርነትና የአምባሳደርነት ቦታዎችን ሊያገኙ እንደሚችሉ።
3. ይህን ድርድር ከተቀበሉ ብርቱካን ሚደቅሳም ከእስር እንደምትለቀቅ።
ፖለቲካ ቁማር ነው። የሽማግሌው ቡድን ከተቃዋሚዎች ጋር የሚያደርገው ውይይትና ድርድር ወዴት እንደሚያመራ በቅርቡ የምንሰማው ይሆናል። መለስ ከሽማግሌዎቹ ጋር ባደረገው ቆይታ፣
“መረራን አጥብቃችሁ ምከሩት!” ሲል ለይቶና አፅንኦት ሰጥቶ መናገሩን ሰምቼያለሁ።Read more...